የኢትዮጵያ የሰላምና የዴሞክራሲ አማራጭ ኃይሎች ምክር ቤት
በታህሳሥ 1986 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ የታቀደው የሰላምና የዕርቅ ጉባዔ ተካሂዷል። በጉባዔው ላይ በሀገር ቤትና ከሀገር ውጭ ያሉ፤ የታገዱና ያልታገዱ፤ ሁለ-ገብ ትግል የሚያካሂዱና በሰላም ብቻ የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የሙያ ማህበራት፤ የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮችና ታዋቂ ግለሰቦችም እንዲሁም የገዥው ፓርቲ ተወካዮች እንዲሳተፉ ጥሪ ተላልፏል።
ምንም እንኳን ሕወሀት/ኢሕአዴግ በዚህ ጉባዔ ላለመገኘት ቢወስንምና ለዚሁ ስብሰባ ከውጭ የመጡትን የድርጅቶች ተወካዮችን አስሮ (አቶ አበራ የማነ አብ ከመኢሶን፣ ወ/ሮ ገነት ግርማና አቶ መስፍን ተፈራ ከኢሕአፓ) ወዲያውኑ ወደ ወህኒ በመወርወርና የተለያዩ ተጽእኖዎች በማድረግ ስብሰባውንም ለማጨናገፍ ቢሞክርም፤ ጉባዔው እንደታቀደው ሊካሄድ ችሏል። ጉባዔው ሰፋ ያለ ቁጥር ያላቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ያቀፈ የአማራጭ ኃይሎች ምክር ቤትን መስርቷል።
ስለ የኢትዮጵያ የሰላምና የዴሞክራሲ አማራጭ ኃይሎች ም/ቤት የተለያዩ ሠነዶች ያላችሁ ትልኩልን ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።