ፓሪስ ሁለት - ኢተፖድኅ
በኤፕሪል 2000 እ.አ.አ. ላይ የተገናኘው የስምንት የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ ኢተፖድኅ የተሰኘውን አካል ለመፍጠር ችሏል። ይህ ስብሰባ የተጠራው ወያኔና ሻዓቢያ ሲያካሂዱት የነበረው ጦርነት በተጋጋለበት አካባቢና በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት፤ በሕዝቡም ውስጥም የዓላማና የትብብር አንድነት እንዲኖር በተጠየቀበት ወቅት ነበር። ተሰብሳቢዎቹ ለሀገሪቷ ችግር የፖለቲካ መፍትሄ ይረዳ ዘንድ የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ አቅርበዋል።
ስለ ፓሪስ ሁለት - ኢተፖድኅ የተለያዩ ሠነዶች ያላችሁ ትልኩልን ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።