YT_TheGeneration

                                                                            YaTewlidTheGeneration

ፓሪስ አንድ ጉባዔ

በመጋቢት 1985 ዓ.ም. እ.አ.አ. ከማርች 11 – 13 1993 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ሰባት ሕብረ ብሔራዊ የፖለቲካ ድርጅቶችና የብሔር እንቅስቃሴዎች በፓሪስ ከተማ ተሰብስበው አንድ ጉባዔ አድርገዋል። ይህ ጉባዔ በሀገር ውስጥ በገዥው ፓርቲ ሕጋዊነት ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችና በገዥው ፓርቲ ሕጋዊነት የተነፈጋቸው ድርጅቶች በአንድ ላይ የመከሩበት ጉባዔ ነበር። የዚህ ገባዔ ዐብይ ዓላማ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ ገምግሞ ለዋና ዋና ችግሮች መፍትሄ የሚገኝበትን ዘዴ ለመሻት አንድ ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያካትት ሁሉን አቀፍ ጉባዔ የሚጠራበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነበር። ስብሰባውን የተካፈሉት ድርጅቶች ሰፊና ጥልቅ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ሁሉንም የሚያካትትና ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ የሰላምና የዕርቅ ጉባዔ ተብሎ የሚጠራ አዲስ አበባ ላይ እንዲጠራ ተስማሙ። ስምምነቱ ወደ ተግባር ሊለውጥ የሚችል አንድ የሰላምና የዕርቅ ኮንፈረንስ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁመው ተለያዩ። ኮሚቴው በተቋቋመ በስምንት ወራት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ የተካሄደውን የሰላምና የዕርቅ ጉባዔ አዘጋጅቷል።         

ስለ ፓሪስ አንድ ጉባዔ የተለያዩ ሠነዶች ያላችሁ ትልኩልን ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

እትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Long Live Ethiopia!

......ያ ትውልድ......
ታሪካችሁ ህያው ነው!

The Generation is Immortal!

 

እኛን ማግኘት/Contact us

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

703 300 4302