ያ ትውልድ ዓርማና መግለጫ፡
የኢትዮጵያ ካርታ፡ በአርማው ላይ የሚታየው የኢትዮጵያ ካርታ ያልተከፋፈለችና የግዛት አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያን (ኤርትራን ጨምሮ ማለት ነው) ያሳያል።
ያ ትውልድ የተዋደቀውና የታገለው ሉዓላዊነቷ ለተጠበቀ ኢትዮጵያና የዴሞክራሲ መብት፡ ፍትኅና የሕግ የበላይነት ለሚጐናጸፍ አንድ ሕዝብ መሆኑን ያንጸባርቃል።
የኢትዮጵያ ካርታ አረንጓዴ ቀለም የያዘው ያ ትውልድ የተነሳው ሀገሩን በልማት ጎዳና ለማሳደግ መሆኑን ያሳያል።
ኢትዮጵያን የደገፉት እጆች፡ ያ ትውልድ በዘር፡ በሃይማኖት፡ በጾታ፡ በዕድሜ ሳይለያይ በጋራ የተነሳው ሀገሩን ኢትዮጵያ ተባብሮና ተደጋግፎ በዕድገትና በልማት ጎዳና ለማንሳት መሆኑን ያሳያል።
የእጆቹ ቀለም ወደ ግራጫ (Gray) መሆኑ ያ ትውልድ ይዞት የተነሳው ቅዱስ ዓላማና ራዕይ በተደረገው ትውልድ የማጥፋት እርምጃ መደብዘዙንዝና የሐዘን ድባብ
ማጥላቱን ያሳያል።
ኢትዮጵያን የከበባት ዘንባባ፡ ዘንባባው ልምላሜን፡ ዕድገትንና ሰላምን ያሳያል። ያ ትውልድ ይዞት የተነሳው ዓላማ አሁንም ህያው መሆኑንና የልጆቿ የሆነች ኢትዮጵያ ወደ ልምላሜና ሰላም ጎዳና
እንደምታመራ ያለውን ራዕይና ተስፋ ያሳያል። ዘንባባውን ያቀፈው (የሚወጣበት) ቀይ ቀለም፡ በትውልድ ማጥፋት ቀይ ሽብር የፈሰሰው ደም፡ ከንቱ እንደማይቀርና
ልምላሜንና ነጻነትን እንደሚያበቅል ያለውን ተስፋ ያሳያል።
ኢትዮጵያን ዙሪያ የከበባት ባንዲራ፡ የኢትዮጵያን ካርታ ዙሪያዋን የከበበው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ የሀገራችን ብሔራዊ መለያችንና የነጻነት ዓርማችን መሆኑን ያንጸባርቃል።
ያ ትውልድ እና The Generation፡ በቅስት መልክ ከላይ በአማርኛ ከታች በእንግሊዘኛ የተጻፈው የተቋማችንን ስያሜና ለያ ትውልድ መታሰቢያነት መቆማችንን ያሳያል።
የያን ትውልድ አኩሪ ታሪክ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁላችንም እንተባበር።
ያ ትውልድ ተቋም