ያ ትውልድ ራዕይና ተልዕኮ
ራዕያችን ፡ ፍትህና የሕግ የበላይነት በሰፈነባት ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ የትውልዳችንን ታሪክ በሚገባ በመጠበቅና ለታሪክ በማኖር ቀጣዩ ትውልድ ሀገሩንና ሕዝቡን አፍቃሪና ታሪክ ተረካቢ ብቁ ዜጋ ሆኖ ማየት።
ተልዕኮአችን ፡ የታሪክ ቅብብሎሽ ይቀጥል ዘንድ ከሚሠሩ ወገኖች ጋር በመተባበር የያን ትውልድ የትግል ታሪክና የተከፈለውን መስዋዕትነት መረጃ ማሰባሰብ፣ ትውልዱ በታሪክ ሲታወስ ይኖር ዘንድ መታሰቢያ ማቆምና የተለያየ ጉዳት የደረሰባቸውን የዚያና የዚህን ትውልድ አባላት መንከባከብ።
ያ ትውልድ ተቋምን ለማቋቋም ምን አነሳሳን?
- የትውልዱ በተለይም የኢሕአፓና የተሰዉት ጋደኞቻቸን ታሪካችው የሚገባውን ያህል ያለመጻፉ፡
- እኛ ያለነው ደግሞ ለተሰዉት ጓዶች የገባነውን ቃል ዳር ሳናደርስ በመቅረታችን (ትግሉን በአሽናፊነት ባለመፈጸማችን) ኅሊናችን ሁሌም ስለሚጠይቀን፡
- በሕይወት ያለን የያ ትውልድ አካላት በአጋጠመን የአካልና የአዕምሮ ጉዳት እርስ በርሳችን እንኳ መጠያየቅና በሚገጥሙ ማናቸውም ማህበራዊ ጉዳዮች መረዳዳትና መተጋገዝ በማስፈለጉ፡
- እኛ በህይወት ኖረን ወላጆቻችንን መጦር ስንችል፡ ሊጦሯቸው የሚችሉ ልጆቻቸውን አጥተው ያለጧሪ የቀሩ ወላጆችን ስናይ ከመጸጸታችን በተጨማሪ ወላጆቻቸውን/አሳዳጊዎቻቸውን ላጡትም ልጆቸ አለኝታ ሳንሆን በመቅረታችን፡
- የእኛ ትውልድ አካላት ዛሬ በሕይወት ያለን ከአለን ልምድና ችሎታ አንፃር በርካታ ልናከናውናቸው የሚገቡን ሕዝባዊና ሀገራዊ ጉዳዮች እያሉ፡ ተበታትነን መቀጠሉ አግባብነት ስለሌለው፡ ዳግም ሊያሰባስቡን በሚችሉ የጋራ ጉዳይ ላይ ለመምከር:
- ለሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታና ለገደብ አልባ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር በኢሕአፓ ጥላ ሥር የተሰለፈን ታሪካችንን ጥላሸት ከሚቀቡና ከሚበርዙ መከላከል በማስፈለጉ፡
- በያ ትውልድና በአሁኑ ትውልድ መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ ቀጣዩ ትውልድ የትግል ታሪካችንን በሚገባ ተረድተው ከእኛ የሚቀስሙትን ትምህርት ያገኙ ዘንድ መሠረት መጣል በማስፈለጉ፡
- ባጠቃላይ የተስዋንለትን ለውጥ ሳናይ በመኖራቸን ሁሌም የተሟላ ደስታ አግኝተን ባለማወቃችን፡ በአቀድነው እንቅስቃሴ ለራሳችን የህሊና እርካታ ለመፍጥር፡ ወዘተ